ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ / ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገ / ኢ / ት / ዋ / ጽ / ቤት በ 2013 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወ / ሴ / መ / ቤት የመኪና መለዋወጫ / ስፔር ፓርት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ግዥ ከ 200,000 / ሁለት መቶ ሺ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተቁ ከ1-4 የተቀሱትንና የሚመለታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ን የማይመለስ ብር 30 / ሰላሳ ብር / ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይቻላል፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ት ዕዛዝ / ሲፒኦ / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገ / ኢ / ል / ት / ጽ / ቤት እና ፍትህ ጽ / ቤት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በየሎት ወይም በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች 12/01/2013 ዓ . ም እስከ 26/01/2013 ዓ . ም በበየዳ ወረዳ ገ / ኢ / ል / ት / ጽ / ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 11 ፡ 30 ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ሳ ጥኑን 27/01/2013 ዓ. ም 4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4 ፡ 30 ሰዓት ሕጋዊ ተጫራቾች ወኪሎ ቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈውን ንብረት በአሸነፈው መጋዘን ማስከረብ የሚል፡፡
- መ / ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሠረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0583272313 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
በሰ / ጎንደር ዞን አስተዳደር ያበያዳ
ወረዳ የ ገ / ኢ / ት / ዋ / ጽ / ቤት
አዲስ ዘመን: ማክሰኞ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ . ም