በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ካምፓኒያችን የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
- ለፕላይውድ እና ቬነር ማምረቻ ማሸኖች መለዋወጫዎች፣
- ፎርክ ሊፍት እና የፎርክ ሊፍቶች ኢንጅን እንዲሁም
- የተለያዩ መለዋወጫዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡፟
- በዘርፉ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
- የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለዕቃዎቹ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / 50,000 ( ሃምሣ ሺህ ብር) በባንክ በተ ረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰ ነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16 ኛው ቀን / ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ ታሽጎ 4:30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል:: ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም::
- የመክፈቻ ቀኑን እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይሆናል::
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመ ከፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ከተጠቀሰው ብዛት ወይም መጠን በታች ቀንሶ መጫረት ውጤት ላያስገኝ ይችላል።
- ኣቅራቢ ድርጅቱ የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ንብረቱን ለካምፓኒው ንብረት ክፍል ያስረከባል።
- የሁሉም እቃዎች ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
- ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበጠበ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 011637 52 71 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/ የተ/ የግል ማህበር
ደ/ብርሀን
አዲስ ዘመን: እሁድ መስከረም 10 ቀን 2013 ዓ . ም