የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፌ/
ፖጤ፡ ቋ/ አ10/2011 ዓ/ ም
የፌዴራል ፖሊስ ጤና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በ2011 ዓ/ም የበጀት ዓመት የተለያዩ መድሃኒቶች ፣ ሪኤጀንቶች እና የህክምና መሳሪያዎችበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ስለሆነ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሥራው ጋራ የተገናኘ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊየንግድ ፈቃድ፣ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ 6 ወር ያላለፈበት፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥየተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር እና ከምግብናመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ዝርዝር መግለጫ የጨረታሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ2:30 – 9:30 ድረስ የፌዴራል ፖሊስ ጤናአገልግሎት ዳይሬክቶሬት ፋይናንስ ማስተባበሪያ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው በመግዛት የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕበማድረግ የተለያዩ መድሃኒቶች ፣ ሪኤጀንቶች እና የህክምና መሳሪያዎች እስከ 26/07/2011 ዓ. ም ከረፋዱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ፌዴራልፖሊስ ጤና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ ቁጥር 32 በመምጣት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ወይምበመልዕክት ሳጥን ቁጥር 21652 መላክ ይችላሉ፡፡ መ/ቤታችን ስለጨረታ ሠነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት አይወስድም፡፡:
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ (BID BOND) የተለያዩ መድሃኒቶች፣ ሪኤጀንቶች እና የህክምናመሳሪያዎች……………20,000.00/ ሃያ ሺህ ብር/ ከ ታወቀ ባንክ የሚሰጥ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በጥሬ ገንዘብና በባንክ ጋራንቲ የምንቀበልመሆናችንን እየገለጽን ጨረታው በ26/07/2011 ዓ. ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በ 4:30 ሰዓት በቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-30-20-19
አድራሻ፡- ልደታ ክ/ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል እና ጨለለቅ ህንፃ መካከል የኢት/ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና አገልግሎት ዳይሬከቶሬት የኢት/ ፌዴ/ ፖ ጤና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
አዲስ ዘመን: አርብ መጋቢት 13 ቀን 2011 ዓ . ም