ለ3 ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
003/2011
የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች አወዳድሮመግዛት ይፈልጋል በመሆኑም፡-
- የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች
- የኮንስትራክሽን ዕቃዎች
- የተለያዩ የደንብ ልብስ
- የትርጉም አገልግሎት
- የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገጃ መኪና ኪራይ አገልግሎት
- የተለያዩ ደንብ ልብሶች ስፌት
- ቢሮችን አፍርሶ ለመጠገንና ለመገንባት
- የሚጫረቱበትን የእቃ ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀንጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በጉ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ንብረት ግዥ አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 19 ዘወትር በስራ ሰዓትበመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የሚጫረቱበትን የዕቃ ዋጋ የሚገልጽ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አስገብቶ ይታሽጋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ናሙና ከጨረታ መክፈቻ ቀናትአስቀድመው ማቅረብ ለሚችሉባቸው እቃዎች እያንዳንዱ ናሙናየማቅረብ ግዴታ አለባቸው፤
- ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት የቢሮ የእቃአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት የታደሰ የንግድ ፍቃድ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ በእያንዳ ንዱ ሎት ማለትም የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ ከብር 5,000.00/ አምስት ሺህ ብር/ ፤የኮንስትራክሽን ዕቃዎች———– ብር5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/ ፤ የተለያዩ የደንብ ልብስ ብር3,000.00 ፣ የትርጉምአገልግሎት——– ብር 2,000.00 ብር እና የፍሳሽ የመፀዳጃ ቤት ማስወገጃ አገልግሎት——– ብር 4,000.00 ያላነሰ የጨረታማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ትዕዛዝ (CPO) እና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርበታል። በእያንዳንዱ ሎት 2% የማስያዝግዴታ አለበት። አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወዲያው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም) ዋስትና /ፐርፎርማንስ ቦንድ (CPO) ጥሬ ገንዘብ /ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ በተጠናቀቀበት 10 ኛው የሥራ ቀን በመ/ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽበዛው ዕለት ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም በዓል ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል፤
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።
- መስሪያ ቤቱ በግዥ ወቅት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የበለጠ ለመረዳት በስልክ ቁጥሮች 0111-56-64-07/0911-99-77-74/0111-57-91-50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የጉለሌ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
አዲስ ዘመን: አርብ መጋቢት 6 ቀን 2011 ዓ . ም