የጨረታ ማስታወቂያ
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ሳሪስ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር02/2011 ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የተለያዩ መድኃኒት እና የህክምና እቃዎች
- የተለያዩ የላብራቶሪ ኤጀንቶች
- ቋሚ የቢሮ እቃ
ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ላይ መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች
1.በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን፡፡
- የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት፡፡
6.እነዚህን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከሳሪስ ጤና ጣቢያክ/ሂ/ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 35 የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን
7.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000 / ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታበማሸግ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10 ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11 ፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥንይታሸጋል፡፡
- ሆኖም ግን የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጣ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
10.ጨረታው የሚከፈተው በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰአት በተገኙበት በግቢው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የመሰብሰቢያአዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
- ሆኖም ግን 11ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ከመ/ቤቱ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች 100% ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሙሉ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን የመስሪያ ቤታችሁን ማህተም በማድረግ እና እያንዳንዱ ገፅ ላይ በመፈረም በታሸገፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
15.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ሳሪስ 3F ፊት ለፊት ከሙኒክ ሆቴል አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡-+011 470 79 77/011 440 41 33
በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ
ክ/ ከተማ ጤና መምሪያ የሳሪስ ጤና ጣቢያ
አዲስ ዘመን: አርብ መጋቢት 6 ቀን 2011 ዓ . ም